ቪዛ እና ሳንቲምፔይ በኢትዮጵያ ዲጂታል ክፍያን ለማቀላጠፍ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

በዓለም አቀፍ ደረጃ በዲጂታል ከፍያዎች የሚታወቀዉ ቪዛ እና ሳንቲም ፔይ ፋይናንሺያል ሶሉሽንስ አ.ማ በብሔራዊ ባንክ ስር ፍቃድ ያለዉ የፖስ ማሽን መሳሪያዎችን ለማሰራጨት የስትራቴጂክ አጋርነት ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ 20 ሺህ በዝቅተኛ ወጪ የሚሸጡ (POS) መሳሪያዎችን በመላው ኢትዮጵያ ለማሰራጨት የሚያስችል ነዉ፡፡

የደቡብ እና የምስራቅ አፍሪካ የቪዛ ኃላፊ ሚካኤል በርነር ፤ ቪዛ በስትራተጂካዊ አጋርነት እና ፈጠራ የኢትዮጵያን ዲጂታል ኢኮኖሚ ለማፋጠን ቁርጠኛ መሆኑን አንስተዉ፤ ከሳንቲም ፔይ ጋር ያለዉ ትብብር የነጋዴዎችን ተቀባይነት ለማስፋት እና የሀገር ውስጥ ንግድን ለማቀላጠፍ እንደሚረዳ አንስተዋል።

የሳንቲም ፔይ ዋና ሥራ አስፈጸሚ ትንሳኤ ደሳለኝ በበኩላቸዉ፤ ይህ ከቪዛ ጋር ያለው ትብብር ለኢትዮጵያ የከፍያ ገጽታ ለውጥ የሚያመጣበት ጊዜ ማሳያ ነዉ ብለዋል።

በተጨማሪም የዲጂታል ክፍያ ተደራሽነት በማስፋት ነጋዴዎችን እና ሻጮችን በተመሳሳይ መልኩ ለማበረታታት እንደሚጠቅምም ገልጸዋል።

ይህ በምስራቅ አፍሪካ በቪዛ የተደገፈ የመጀመሪያው የፋይናንስ አጋርነት ፕሮግራም ሲሆን፤ በቪዛ ለኢትዮጵያ የዕድገት ስትራቴጂ የPOS ስርጭትን ለማሳደግ፣ የነጋዴዎችን ተቀባይነት ለማስፈን እና የፋይናንስ አካታችነትን ለማጎልበት ቁልፍ ምዕራፍ መሆኑም ተገልጿል።

ለዓለም አሰፋ

መስከረም 20/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *