በሺዎች የሚቆጠሩ የፌዴራል ሰራተኞች የአሜሪካ መንግስት ቁልፍ አገልግሎቶችን በመዝጋቱ ምክንያት ደመወዝ ሳይከፈላቸው ስራ ማቆማቸዉ ተገለጸ

ከ2018 መጨረሻ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተው ይህ ሁኔታ፤ ሁሉንም ሳይሆን አንዳንድ የአሜሪካ መንግስት አገልግሎቶችን ለጊዜው ሊያቆም ይችላል ተብሏል።

ቀደም ሲል ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ሁኔታዉ በዚህ ከቀጠለ የፌዴራል ሰራተኞች ላይ በጅምላ የማይመለስ ከስራ ማባረር እንደሚያስከትል አስጠንቅቀው ነበር።

አንዳንዶቹ ያለ ክፍያ ቢሆንም አስፈላጊ ሰራተኞች መስራታቸውን ይቀጥላሉ፤ ነገር ግን ሌሎች የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ ሳይከፈላቸው በእረፍት ላይ ናቸው ተብሏል።

በኮንግረስ ውስጥ ያሉ ፖለቲከኞች ግን ደመወዝ ይከፈላቸዋል ነዉ የተባለዉ።

ሪፐብሊካኖች እና ዴሞክራቶች ከ1መቶ ሴናተሮች የ60ዎቹ ድጋፍ የሚያስፈልገው ረቂቅ ህግ ባለመጽደቁ እርስ በእርስ እየተወነጃጀሉ ነው ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።

እስከዳር ግርማ

መስከረም 21/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *