14ተኛዉ የኢትዮ ፖልተሪ ኤክስፖ ÷10ኛዉ የአፍሪካ እንስሳት አዉደርዕይ በተጨማሪም 5ተኛዉ የአፒካልቸር እና አኳካልቸር ኢትዮጵያ አለም አቀፍ ንግድ ትርኢት ሊካሄድ ነዉ፡፡
በመጪዉ ጥቅምት 20 እስከ 22 ድረስ በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ዛሬ አዘጋጆቹ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።
ተያይዞም በኢትዮጵያ ቀዳሚ ነዉ የተባለዉ የእንስሳት ዘርፍ አዉደ ርዕይ እና ጉባኤም የሚካሄድ እንደሆነ ነዉ አዘጋጆቹ የገለፁት።
በሚካሄደው ሁሉን አቀፍ የእንስሳት ሀብት እሴት ሰንሰለት ንግድ ትርኢት እንደሚኖርም ነዉ በመድረኩ የተገለፀዉ።
የእንስሳት መኖን፣ የእንስሳት ጤናን፣ ዶሮ እርባታን፣ ወተት፣ ስጋ፣ እንቁላል፣ አሳ ሃብት፣ ንብ እርባታን እንዲሁም ባዮ ኢነርጂ ላይ ትኩረት ይደረጋል ተብሏል።
በዚህም የኢትዮ ዶሮ ኤክስፖ እንዲሁም የአፍሪካ የእንስሳት ሀብት አዉደ ርዕይ እና ጉባኤ እንደሚኖር ተጠቁሟል።
የኢትዮጵያ የአሳ እና ማር ኤክስፖ በሚካሄደው ስነስርዓት ላይ ዘርፉ የሚተዋወቅበት እድል የሚፈጠርበት ይሆናል ተብሏል።
ይካሄዳል በተባለዉ በዚህ ኤክስፖ ከዘርፉ ከፍተኛ ተሳትፎ አላቸዉ የሚባሉ ተሳታፊዎች የሚታደሙበት እንደሆነ በተሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ተነግሯል።
በዚህም በሀገሪቱ ያሉ የአንድ ቀን ጫጩት አቅራቢዎች እና መኖ አምራቾች ተሳትፎ የሚጠበቅበት እንደሆነ ተገልጿል።
ከ14 ሀገራት የተውጣጡ ከ80 በላይ ዓለምቀፍ የቴክኖሎጂ እና ግብዓት አቅራቢዎች እንዲሁም ታዋቂ የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች እንደሚሳተፉበት ነዉ የተነገረዉ፡፡
ዝግጅቱን 14ኛው የኢትዮ የዶሮ እርባታ ኤክስፖ (ETHIOPEX) እና 10ኛው የአፍሪካ የእንስሳት እርባታ ኤግዚብሽንና ኮንግረስ (ALEC) በጋራ የሚያካሂዱት ሆኗል።
ልምድና ተሞክሮ በማጋራት፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ እንዲሁም ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት በዘርፉ ዕድገት ለመጨመር የታለመለት መሆኑን በመግለጫዉ ተጠቁሟል።
ቁምነገር አየለ
ጥቅምት 04/2018 ዓ.ም
