ሐማስ ረቡዕ ዕለት የተጨማሪ ሁለት ታጋቾችን አስከሬን ማስረከቡን ገልጾ፣ ነገር ግን የሌሎችን አስከሬን ከጋዛ ፍርስራሾች ውስጥ ለማውጣት ተጨማሪ ጊዜ እና የዘመኑ መሳሪያዎች ያስፈልጉኛል አለ።
የቡድኑ ወታደራዊ ክንፍ ባወጣው መግለጫ ላይ ለሰላም ስምምነቱ ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቆ እስካሁን ማስረከብ የቻለው የታጋቾች አስከሬን ሊደርስባቸው የቻላቸውን ብቻ መሆኑን ገልጿል።
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሐማስ ለስምምነቱ ተገዥ ካልሆነ እስራኤል በጋዛ የምታካሄደውን ወታደራዊ ዘመቻ ልትቀጥል ትችላለች ብለዋል።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በበኩሉ በቀይ መስቀል በኩሉ የታጋቾችን አስከሬን መቀበሉን ገልጾ ማንነታቸውን የመለየት ሥራ ይቀራል ብሏል።
የእስራኤል ጦር ሕዝቡ በትዕግሥት እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርቦ “የታጋቾቹን ማንነት የማረጋገጥ ሥራ ተሰርቶ በመጀመርያ ለቤተሰቦቻቸው እንደሚያሳውቅ” ገልጿል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
ጥቅምት 06/2018 ዓ.ም
