አቢሲኒያ ባንክ ባለ 2 መኝታ ቤት የሚያሸልመዉን የዕጣ ቁጥር ይፋ አደረገ

ባንኩ አቢሲንያ የድጂታል አማራጮችን በመጠቀም ግብይት ለፈጸሙ ደንበኞች ያዘጋጀው (Merchant Engagement Campaign) መጠናቀቁን ተከትሎ ባካሄደዉ የዕጣ ማውጣት መርሐ-ግብር ነዉ ይፋ ያደረገዉ።

በዚህም አሸናፊዉ የዕጣ ቁጥር 0001801876786 መሆኑን በብሄራዊ ሎተሪ የእድል አዳራሽ በተካሄደዉ የዕጣ ማዉጣት ላይ መገለጹን ጣቢያችን ተመልክቷል።

በብሄራዊ ሎተሪ አዳራሽ በተደረገዉ የዕጣ ማዉጣት ስነ ስርዓት ባለእድለኛዉ ይፋ ሲሆን፤ መሀመድ የተባለ አያት አካባቢ የሚኖር ግለሰብ እንደሆነም ሰምተናል።

ከሚያዝያ 17 /2017 ዓ.ም እስከ መስከረም 18/2018 ዓ.ም ጀምሮ በዲጂታል ግብይት ሲያደርጉ የነበሩ ደንበኞችን በእጣዉ ውስጥ እንደተካተቱ ተነግሯል።

የዲጂታል መተግበሪያን በመጠቀም የሚደረገዉ ግብይት ለ5 ወራት ሲያካሄድ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን፤ ለባለ ዕድለኛዉ የባለ 2 መኝታ ቤት አፓርትመንት የሚስገኘው እጣ ወጥቶ ተጠናቋል።

በዚህ ዕጣ ላይ ከ3 ሚሊየን በላይ የዕጣ ቁጥሮች ለደንበኞች መሰጠቱም ተሰምቷል።

ለዓለም አሰፋ

ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *