ኢትዮጵያዊቷ ደራሲ ማክዳ አርሺ በ10 ወራት ውስጥ ለአራተኛ ጊዜ አለም አቀፍ ሽልማት ተሸላሚ ሆነች።

ማክዳ፤ “Shining As I Am” (እንዳለሁ አበራለሁ) በተሰኘው የልጆች መጽሐፍ ነው “International Impact Book Award” ዘርፍ የ2025 አሸናፊ የሆነችው።

ባሳለፍነው ቅዳሜ በአሜሪካ አሪዞና ግዛት ፊኒክስ ከተማ በተካሄደ ታላቅ የሽልማት ስነ ስርዓት ላይ ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ ፈጣሪ መጽሐፍ ሽልማት ዘርፍ ይሄው “Shining As I Am” (እንዳለሁ አበራለሁ) መፅሃፍ አሸናፊ ሆኖ ደራሲዋ ሽልማቷን ተቀብላለች።

Shining As I Am” (እንዳለሁ አበራለሁ)፤ በሚያስተላልፈው ጠንካራ መልዕክት እና በልጆች ሥነ-ጽሑፍ ላይ ባበረከተው አስተዋጽኦ ለዚህ ክብር መብቃቱ ተገልጿል። ይህ ድል ለደራሲ ማክዳ አርሺ ትልቅ ስኬት ከመሆኑም ባሻገር፣ የመጽሐፉ መልዕክት በዓለም ዙሪያ ላሉ በርካታ አንባቢያን እንዲደርስ ያግዛል።

ደራሲዋ በዚሁ “Shining As I Am” (እንዳለሁ አበራለሁ) በተሰኘ መፅሃፏ አንድ አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሶስት አለም አቀፍ ሽልማቶችን ያገኘች ሲሆን ይኸኛው አራተኛዋ ሽልማት ሆኗል።

“International Impact Book Award” በዓለም ዙሪያ በአንባቢያን ሕይወት ላይ በጎ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ፣ አዎንታዊ ለውጥን የሚያበረታቱ እና ጠቃሚ መልዕክቶችን የሚያስተላልፉ መጽሐፍትን እውቅና የሚሰጥ ዓለም አቀፍ ተቋም ነው። አውስትራሊያ እና እንግሊዝን ጨምሮ ከተለያዩ የዐለም ክፍል የመጡ ደራሲያንም ተሳትፈውበታል።

ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *