የቻይናው እጅግ ዘመናዊ የአውሮፕላን ተሸካሚ ፉጂያን፤ ፕሬዝዳንቱ በተገኙበት ታላቅ የመርከብ ሥነ ሥርዓት ከተከበረ ከጥቂት ቀናት በኋላ ወደ አገልግሎት መግባቱ ተዘግቧል።
የአገሪቱ ሶስተኛ የጦር መርከብ የሆነው ፉጂያን፤አውሮፕላኖች በከፍተኛ ፍጥነት እንዲወነጨፉ የሚያስችል ኤሌክትሮማግኔቲክ መሳሪያ የተገጠመለት ነው።
በአሁን ወቅት በዓለም ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው መርከቦችን በመያዝ ትልቅ የባህር ኃይል ባለቤት ለሆነችው ቤጂንግ፤ የመርከቧ ስራ መጀመር ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል ነዉ የተባለዉ፡፡
ቻይና በፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ዘመን የባህር ኃይሏን በከፍተኛ ፍጥነት እያሰፋች ሲሆን፤ አሜሪካ እና አጋሮቿም ፍጥነታቸውን እንዲቀጥሉ ጫና ፈጥራለች።
አዲሱ መርከብ በኤሌክትሮማግኔቲክ መሳሪያ እና ጠፍጣፋ የበረራ ወለል ሶስት የተለያዩ አውሮፕላኖችን ማምጠቅ እንደሚችል የአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡
በአገር ውስጥ የተገነባው መርከብ ከባድ የጦር መሳሪያዎችንና የነዳጅ ጭነቶችን የያዙ አውሮፕላኖችን በመያዝ የጠላት ኢላማዎችን ከሩቅ መምታት የሚችል ሲሆን፤ ይህም በሩሲያ ከተገነቡት የመጀመሪያዎቹ ሁለት አዉሮፕላን ተሸካሚ መርከቦች የበለጠ ኃይለኛ ያደርገዋል።
የቻይና ሚዲያዎች ፉጂያንን የቻይና የባህር ኃይል ልማት ‹‹ትልቅ ምዕራፍ›› ሲሉ አወድሰውታል።
አሜሪካ ከፉጂያን ጋር ተመሳሳይ የኤሌክትሮ ማግኔቲክ ካታፑልት ሲስተም ያለው የአውሮፕላን ተሸካሚ ያላት ብቸኛዋ ሀገር ነች ሲል የዘገበዉ ቢቢሲ ነዉ።
ሀና ሰይፉ
ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም
