AI የሚለውን ሁሉ በጭፍን አትመኑ- የአልፋቤት ኩባንያ ሀላፊ ሰንደር ፒቻይ

ሰዎች የAI መሳሪያዎች የሚነግራቸውን ሁሉ በጭፍን ማመን የለባቸውም ሲሉ የጎግል እናት ኩባንያ አልፋቤት ኃላፊ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ልዩ ቃለ ምልልስ ያደረጉት ዋና ስራ አስፈፃሚው ሱንዳር ፒቻይ፤ የAI ሞዴሎች ለስህተት የተጋለጡ መሆናቸውን በመግለፅ ሰዎች እነዚን መተግበሪያዎች ከሌሎች አጋዥ መሳሪያዎች ጋር እንዲጠቀሙ አሳስበዋል፡፡

በAI ቴክኖሎጂ ላይ ብቻ ከመተማመን ይልቅ የበለፀገ እና ሰፊ የሆነ የመረጃ ስነ-ምህዳርን መፍጠር ወይንም መፈለግ ተገቢ ነውም ብለዋል፡፡

ለዚህም ነው ሰዎች ሌሎች የጎግል ፍለጋ አማራጮችን የሚጠቀሙት ያሉት ሀላፊው፤ የበለጠ ትክክለኛ መረጃን ለማቅረብ የተመሰረቱ ሌሎች ምርቶችም አሉን ነዉ ያሉት፡፡

አንዳንድ ባለሙያዎች እንደ ጎግል ላሉ ትልልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የመሳሪያዎቻቸውን ውጤት እንዲፈትሹ እና እንዲያጣሩ ከመጋበዝ ይልቅ ስርዓቶቻቸውን ይበልጥ አስተማማኝ ማድረግ ላይ ማተኮር አለባቸው ብለዋል።

የAI መሳሪያዎች ጠቃሚዎች ናቸው፤ የፈጠራ ስራዎችን ለመስራት ያግዛሉ ነገር ግን ሰዎች እነዚህን መሳሪያዎች ምን ላይ ጥሩ እንደሆኑ በመለየት መጠቀምን መማር አለባቸው ፤ሁሉንም በጭፍን ማመን ተገቢ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በተቻለ መጠን AI ትክክለኛ መረጃ እንዲሰጥ በምንሰራው ስራ እንኮራለን፤ ነገርግን አሁን ያለው ዘመናዊ የAI ቴክኖሎጂ ለአንዳንድ ስህተቶች የተጋለጠ ነው ብለዋል፡፡

ድርጅታችን ስህተት ሊሰራ እንደሚችል ለተጠቃሚዎች ያሳዉቃል፤ ይህም ግን ከትችት አያድንም ማለታቸዉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ሀና ሰይፉ

ህዳር 09/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *