ትራምፕ ከዢ ጋር በስልክ ከተነጋገሩ በኋላ በሚያዝያ ወር ቻይናን እንደሚጎበኙ ተናገሩ

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሚያዚያ ወር ቤጂንግን ለመጎብኘት መስማማታቸው አስታውቀዋል፡፡

ሁለቱ መሪዎች ያደረጉትን የስልክ ንግግር ተከትሉ የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ በሚቀጥለው ዓመት መጨረሻ ላይ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እንዲያደርጉ እንደጋበዟቸው ትራምፕ ገልጸዋል፡፡

በደቡብ ኮሪያ ከአንድ ወር ገደማ በፊት የተገናኙት ትራምፕ እና ዢ በተለያዩ ጉዳዩች ላይ መወያየታቸውን ፕሬዝደንት ትራምፕ እና የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቀዋል ፡፡

“ከቻይና ጋር ያለን ግንኙነት እጅግ በጣም ጠንካራ ነው!” ሲሉ ትራምፕ በTruthSocial ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።

የቻይና አዲስ የመንግስት ኤጀንሲ ሁለቱም ሀገራት “በእኩልነት፣ በመከባበር እና በጋራ ጥቅም ላይ በመመስረት በትክክለኛው አቅጣጫ ወደፊት መጓዝ አለባቸው” የሚል መግለጫ አውጥቷል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

ህዳር 16/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *