በድሬደዋ ከተማ ስር ያሉ አብዛኞቹ የከተማዉ መንደሮች በኘላስቲክ ቆሻሻ  እየተፈተኑ እንደሚገኝ ተገለፀ።

በከተማዋ በተለይም በቀፊራ እና ለገሃሬ እንዲሁም በደቻቱ ወንዝ መተላለፊያ አካባቢ ስስ ፌስታል እና መሰል ደረቅ ቆሻሻ በስፋት የሚገኘባቸዉ መሆኑን ሰምተናል

ወደ አንድ ሚሊየን እየተጠጋ የሚገኘዉ  የድሬደዋ ከተማ የህዝብ ቁጥር የነዋሪዉ የአኗኗር ዘይቤ ለአካባቢ ብክለቱ በምክንያትነት ተጠቅሷል።

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ÷ ደን እና የአየር ንብረት ባለስልጣን የአካባቢ ህግ ተከባሪነት ግምገማ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ደረጄ አቢች በከተማዉ ከኘላስቲክ ቆሻሻ ጋር ተያይዞ ችግር መስተዋሉን ነግረዉናል።

ከኢትዩ ኤፍኤም ጋር ቆይታ የነበራቸዉ ሃላፊዉ ለተለያዩ አላማዎች ነዋሪዎች የሚጠቀሟቸዉ እነዚህ የኘላስቲክ ምርቶች በየአካባቢዎቹ መታየታቸዉን ገልፀዋል።

የታሸጉ ዉሃዎችን በብዛት ከመጠቀም እንዲሁም ነዋሪዉ ለመያዥነት የሚያጠቀማቸዉ  ላስቲኮች በአካባቢዎቹ በከፍተኛ መጠን እየታዩ እንደሚገኝ ሰምተናል

ለዚህ ማረጋገጫዉ  ደግሞ የከተማዉ የመጨረሻ ቆሻሻ ማስወገጃ ላይ በርካታ የኘላስቲክ ምርት መገኘቱ መሆኑን ሀላፊዉ ያስረዳሉ።

ይህ ችግር ከተማዋን አቋርጠው በሚሄዱ ደረቅ የአሸዋ ወንዞች  እና በማእከል ደቻቱ ወንዝ መተላለፊያ ÷በጎሮ መልካሳ እና ቀፊራ ÷ ለገሃሬ እና ጋራዥ እንዲሁም ክፍት የገበያ ቦታዎች ላይ እየታየ እንደሚገኝ ሰምተናል

አቶ ደረጄ እንደገለፁት በድሬደዋ ከተማ የቡቲጂ ወንዝ ተፋሰስ ዙሪያ ለአንድ ጊዜ ጥቅም ላይ ከሚዉለዉ ፌስታል በተጨማሪ በሌሎች ደረቅ ቆሻሻ ጭምር  ከፍተኛ ብክለት እንዳጋጠመዉ ተናግረዋል።

በከተማዋ የሚስተዋለዉ በንክሻ የሚተላለፉ ወባ እና መሰል በሽታን ለመከላከል ጥረት በማድረግ ዉስጥ የወንዙን ደረቅ ቆሻሻ በማስወገድ ምክንያት በወንዙ ውሃ በመከማቸቱ ለትንኝ መራቢነት ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ እንደሚገኝ ተገልፆል ።

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ÷ ደን እና የአየር ንብረት ባለስልጣን የአካባቢ ህግ ተከባሪነት ግምገማ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ደረጄ አቢች ደረቅ ቆሻሻን መልሶ መጠቀም ዙሪያ ስራዎች መኖራቸዉን ጠቁመዋል።

በደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ላይ ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ የንቅናቄ ስራዎች  እየተሰራ እንደሚገኝ ነግረዉናል።

ቁምነገር አየለ

ህዳር 22/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *