የዩክሬን እና የአሜሪካ ተደራዳሪዎች ከሞስኮ ዉይይት በኋላ በአሜሪካ ሊገናኙ ነው ተባለ

የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ እና የዩክሬን ብሔራዊ የጸጥታ ምክር ቤት ኃላፊ ሩስተም ኡሜሮቭ በማያሚ እንደሚወያዩ ዋይት ሀውስ ማረጋገጫ ሰጥቷል።

ስብሰባው የመጣው ዊትኮፍ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሞስኮ አምስት ሰዓት የፈጀ ነገርግን ጦርነቱን በማስቆም ረገድ ምንም ዓይነት ስምምነት ያለመጣ ድርድር ካደረጉ በኋላ ነዉ፡፡

የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ውይይቶቹ ምክንያታዊ በሆነ መልኩ ጥሩ ናቸው ነገር ግን ምን ሊፈጠር እንደሚችል ለመናገር አይቻልም ብለዋል፡፡

የዩክሬን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንድሪ ሲቢያ፤ ሩሲያ ደም መፋሰስን ማቆም አለባት ሲሉ ፑቲንን የአለምን ጊዜ እያባከኑ ነዉ ሲሉ ከሰዋል።

ቀደም ብለዉ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በአሜሪካ እና በዩክሬን ተደራዳሪዎች መካከል በሚቀጥሉት ቀናት ስብሰባ እንደሚካሄድ ተናግረዉ ነበር፡፡

ዘለንስኪ በኤክስ ገጻቸዉ ላይ፤ በአሁኑ ጊዜ ዓለም ጦርነቱን ለማቆም እውነተኛ ዕድል እንዳለ በግልጽ ይሰማዋል ብለዋል።

ነገር ግን ድርድሩ እንዲሳካ በሩሲያ ላይ ግፊት መደረግ አለበት ሲሉ አክለዋል እንደ ቢቢሲ ዘገባ።

ቃልኪዳን ተክሉ

ህዳር 25/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *