የሀገሪቱ ባለሥልጣናት መንቀጥቀጡን ተከትሎ ተጨማሪ የድህረ መንቀጥቀጦች ሊከሰቱ እንደሚችሉ በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው።
ባለሥልጣናት እንደገለጹት ከመንቀጥቀጡ በኋላ በሰዎች ላይ የደረሰውን ጉዳት እየገመገሙ ነው።
በዜና ዘገባዎች መሠረት ቢያንስ 30 የሚደርሱ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል የተባለ ሲሆን፤ አብዛኛው ጉዳት የደረሰው በሚወድቁ ነገሮች ነው።
ከመሬት መንቀጥቀጡ በኋላ የጃፓን የሚቲዮሮሎጂ ሱናሚ ሊከሰት እንደሚችል ቢያስጠነቅቅም፤ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ማስጠንቀቂያዎቹን ዝቅ አድርጎ ዛሬ ጠዋት ሁሉንም የሱናሚ ማስጠንቀቂያዎች አንስቷል።
በመንቀጥቀጡ ምክንያት በአካባቢው የሚገኙ አንዳንድ የባቡር አገልግሎቶች ለጊዜው ታግደው የነበረ ሲሆን፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤቶችም የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦ ነበር።
ባለሥልጣናት አሁንም በሚቀጥሉት ቀናት ተጨማሪ ድህረ መንቀጥቀጦች ሊከሰቱ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።
ሱፊያን አህመድ
ህዳር 30/2018 ዓ.ም
