አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ለ14 አባላቱ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን አስረከበ

ከፌደራል ህብረት ስራ ኮሚሽን ፈቃድ አግኝቶ ላለፉት 13 ዓመታት በተለያዩ የሃገራችን አካባቢዎች የፋይናንስ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር፤ በዛሬው ዕለት ለአባላቱ 14 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን አስረክቧል፡፡

ማህበሩ በኢትዮጵያ የመኪና ገበያ ላይ ከሚንቀሳቀሰው “ኖታ ካርስ” ጋር በመተባበር ነዉ የርክክብ መርሐ ግብሩን ያደረገዉ፡፡

አባላቱ የዚህ እድል ተጠቃሚ የሆኑት በተመጣጣኝ ቁጠባና በአነስተኛ የወለድ ምጣኔ በተመቻቸ የብድር ስርዓት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ማህበሩ በተለይም አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲሁም በንግድና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ አካላትን በመደገፍ ለስራ እድል ፈጠራ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ይታወቃል፡፡

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ተደራሽ ለማድረግ የተሰራው ይህ ስራ፤ መንግስት የነዳጅ ወጪን ለመቀነስ እና የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል ያስቀመጠውን አቅጣጫ የሚደግፍ መሆኑም በመድረኩ ተነስቷል፡፡

ልዑል ወልዴ

ታህሳስ 02/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *