ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ ለሁለት ቀናት ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

ናሬንድራ ሞዲ አዲስ አበባ ሲደርሱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር በኢንቨስትመንት እና በሳይበር ደህንነት ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ ተጠቁሟል

ህንድ በመጪው የፈረንጆቹ 2026 የብሪክስ ጉባዔን በሊቀመንበርነት ለመምራት በዝግጅት ላይ ባለችበት ወቅት፣ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ታሪካዊ የተባለለትን ጉብኝት ከዛሬ ታህሳስ 7 እስከ 8/2018 ዓ.ም ድረስ እንደሚያደርጉ ተዘግቧል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ በጉብኝታቸው ወቅት በኢትዮጵያ በሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ላይ ንግግር እንደሚያደርጉም ይጠበቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ በ15 ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያን የሚጎበኙ የመጀመሪያው የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸዉ፡፡

ታህሳስ 07/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *