የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ያስገነባውን ፕሪሚየር ላውንጅ አስመረቀ።

ይህ ፕሪሚየር ላውንጅ በአንድ ጊዜ አንድ ሺህ ተጓዦችን ማስተናገድ የሚችል የፕላቲኒየም ደረጃ ያለው ነው።

በተጨማሪም አየር መንገዱ የብር እና የወርቅ ደረጃ ያላቸው ላውንጆች አሉት።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፥ ይህ ፕሪሚየር ላውንጅ ለደንበኞች ምቾት ያለውን አገልግሎት እንዲያገኙ ከማድረስ ባሻገር 16 የተለያዩ አገልግሎት የሚሰጡ ክፍሎችን እንደያዘ ገልፀዋል።

አየር መንገዱ አገልግሎቱን በጥራትና በልህቀት ጭምር አጠናክሮ መቀጠሉንም ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ መስፍን ተናግረዋል።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥና የአየር መንገዱ የቦርድ ሰብሳቢ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ በበኩላቸው፥ ተቋሙ እየሰራ ያለው ስራና እየደረሰበት ያለው ከፍታ የሚደነቅ መሆኑን አንስተዋል።

የውልሰው ገዝሙ

ታህሳስ 08/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *