አገልግሎቱ የደንበኛና የአሽከርካሪ መለያ ኮድ የፈጠረ መሆኑን አስታውቋል።
እንዲሁም አሽከርካሪው ከተሳፋሪው ጋር በዋጋ ተራድሮ በተስማሙበት ክፍያ መጓዝ የሚያስችል አሰራር ያለዉ ነው ተብሏል።
ከዚህ በተጨማሪም ተሳፋሪዎች በራሳቸው ጉዞ ማስጀመር እንዲችሉ በማድረግ በዋጋ ታሪፍ ላይ ታአማኒነትን ለማረጋገጥ እንደሚያግዝ ተጠቅሷል።
አገልግሎቱ ከአዲስ አበባ ውጪ ተደራሽ እንደሚሆን የተገለፀ ሲሆን፤ በቅርቡም በአዳማ ከተማ ይጀመራል ተብሏል።
ዶንኪ ድራይቭ ከኦሮሚያ ባንክ ጋር ስምምነት በመፈጸም አሽከርካሪዎች ለሚያጋጥማቸው የነዳጅ፣ የመለዋወጫ እና አጠቃላይ ድንገተኛ የገንዘብ እጥረት በቀላሉ ያለተያዥ ከወለድ ነጻ የብድር አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታ እንደሚፈጥር ተነስቷል።
ሐመረ ፍሬው
ታህሳስ 08/2018 ዓ.ም
