“የኔም ልጆች ናቸዉ” በሚል መሪ ቃል ለ50 ሺህ ህፃናት እና ቤተሰቦቻቸው ድጋፍ የማሰባሰቢያ ዝግጅት ሊካሄድ ነው

ለዚሁ በጎ ተግባርም ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ከድጋፍ አሰባሳቢ የበጎ ፈቃደኛ አንጋፋ ሴት ጋዜጠኞች፣ ደራሲያት እና ምሁራን ጋር ጥምረት ፈጥረዋል።

50ሺህ ህጻናትን ወደ ተማሪ ቤት ለመመለስ የሚያስፈልገው አንድ ቢሊዮን ብር ነው።በትግራይ፣ በሶማሊያ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ እና በአፋር በከፋ ችግር ውስጥ ለሚገኙ እና ለጎዳና ተጋላጭ ህጻናት እና ቤተሰቦቻቸው ድጋፍ ይደረጋል ተብሏል፡፡

የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መሥራች ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ በመግለጫው ላይ እንዳሉት በዚህ ወቅት በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ባለው ማህበራዊና ፓለቲካዊ ቀውሶች ምክንያት ከ7ሚሊየን በላይ ህጻናት ከትምህርት ገበታቸው ላይ ርቀዋል።

የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱትም በኢትዮጵያ 43% የሚሆነው ህዝብ በድህነት ውስጥ የሚገኝ ነው።በከተሞች አካባቢ ያለው የድህነት ተጋላጭነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱም ህፃናት ፣እናቶች፣ ሴቶች እና አረጋዊያን ለከፋ ህይወት ተዳርገዋል ብለዋል።

በመሆኑም ከዚህ አስከፊ ኑሮ እንዲወጡ የመንግስትን እና የሌሎች ባለድርሻ አካላት ሰፊ ትብብርና ቅንጅታዊ ሥራን ይጠይቃል ብለዋል።

ይህንን አሳሳቢ ጉዳይ መነሻ በማድረግ ጥምረቱ “የእኔም ልጆች ናቸው” በሚል መሪ ቃል ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ቀደም ብሎ የጀመረውን የህፃናት ስፖንሰርሽፕ ድጋፍ በማስፋት ከ50 ሺህ በላይ ህፃናትን ለማገዝ ንቅናቄዉን በይፋ አስጀምሯል፡፡

ይህንን ትልቅ ማህበራዊ ኃላፊነት ለመወጣት ልዩ የበይነ መረብ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ከጥር 20 እስከ ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ይካሄዳል ተብሏል፡፡

ታህሳስ 08/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *