የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሼባ ማይልስ እና አኮያ ፕሮፐርቲስ ስምምነት ተፈራረሙ።

አርቲስት እፀህይወት አበበ የድርጅቱ ብራንድ አምባሳደር ሆናለች።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሼባ ማይልስ እና አኮያ ፕሮፐርቲስ የደንበኞቻቸውን ተጠቃሚነት የሚያሳድግ የስትራቴጂካዊ አጋርነት ስምምነትን ተፈራርመዋል።

ታህሳስ 7 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል በተከናወነው የፊርማ ስነ-ስርዓት፣ የአየር መንገዱን የሽልማት መርሃ-ግብር (ShebaMiles) ከሪል እስቴት ግብይት ጋር የሚያስተሳስር ስምምነት ተደርጓል።

በዚህ ስምምነት መሰረት በአኮያ ፕሮፐርቲስ እየተገነቡ ያሉ ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶችን እና የንግድ ሱቆችን የሚገዙ ደንበኞች፣ የስታር አሊያንስ (Star Alliance) አባል ከሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሼባ ማይልስ የጎልድ አባልነት ሽልማት በክብር የሚያገኙ ሲሆን ይህም ደንበኞች በኢንቨስትመንታቸው ልክ የአየር መንገዱን ጥቅማጥቅሞች እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ተብሏል ።

ይህ ስምምነት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሼባ ማይልስ እና የሪል እስቴት ዘርፍ መካከል ያለውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑ ተመልክቷል።

በዚሁ መርሃ-ግብር ላይ አኮያ ፕሮፐርቲስ በተለያዩ ፊልሞችና የጥበብ ስራዎቿ የምትታወቀውን አርቲስት እፀህይወት አበበን የድርጅቱ የብራንድ አምባሳደር አድርጎ በይፋ አስተዋውቋል።

አርቲስቷ የድርጅቱን ገፅታ በመገንባትና የምርት ስሞቹን ለህዝብ በማስተዋወቅ ረገድ ግንባር ቀደም ስራዎችን እንደምትሰራ ተገልጿል።

ከ230 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረው አኮያ ግሩፕ፣ በውስጡ የተለያዩ ታላላቅ ድርጅቶችን አቅፎ የያዘ ግዙፍ ተቋም ነው። ከእነዚህም መካከል፦አኮያ ፕሮፐርቲስ፦ በሪል እስቴት ዘርፍ ዘመናዊ ቤቶችን የሚያቀርብ፣አኮያ ኮፊ፦ በቡና ምርትና ኤክስፖርት ላይ የተሰማራ፣አኮያ ሞተርስ፦ በተሽከርካሪ ግብይት ዘርፍ የሚንቀሳቀሱ ይገኙበታል።

ታህሳስ 08/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *