ዘሌንስኪ የሰላም ስምምነቱ 90 በመቶ ዝግጁ መሆኑን ገለፁ

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ከሩሲያ ጋር የሚደረገውን ጦርነት ለማስቆም የሚያስችለዉ የሰላም ስምምነት 90 በመቶ ዝግጁ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ የአዉሮፓዉያኑን አዲስ ዓመት አስመልክቶ ያደረጉት ንግግር በአብዛኛው የሞስኮን ሙሉ ወረራ በመቃወም ላይ ያተኮረ ነበር።

ዘሌንስኪ እንዳሉት የቀረው 10 በመቶ ስምምነት ለአራት ዓመታት የዘለቀውን ግጭት ለማስቆም የዩክሬንን እና የአውሮፓን እጣ ፈንታ ይወስናል ብለዋል።

ረቡዕ ዕለት ሞስኮ ዩክሬን በሰሜን ምዕራብ ሩሲያ በሚገኘው ቫልዳይ ሐይቅ ላይ የሚገኘውን የፑቲን የግል ቤት ኢላማ ለማድረግ ድሮኖችን እንደተጠቀመች የሚያሳይ ማስረጃ ይፋ አድርጋለች፤ ኪቭ ግን ክሱን አጥብቃ አስተባብላለች።

ሩሲያ በተከሰተው ክስተት ምክንያት በሚካሄደው የሰላም ድርድር ላይ ያላትን አቋም እንደምትገመግም አስታዉቃለች፡፡

ሞስኮ በአሁኑ ጊዜ 75በመቶ የሚሆነውን የዶኔስክ ክልል እና 99 በመቶ የሚሆነውን የጎረቤት ሉሃንስክ ክልል ትቆጣጠራለች። ሁለቱ ክልሎች በጋራ ዶንባስ በመባል ይታወቃሉ እንደ ቢቢሲ ዘገባ።

ቃልኪዳን ተክሉ

ታህሳስ 23/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *