ከኢትዮጵያ ገበሬዎች የተገኙ የጥራጥሬ እህሎችን በምግብነት አሽጎ ለገበያ ማቅረቡን ዳቺ ማኑፋክቸሪንግ ገለጸ

ከኢትዮጵያ ገበሬዎች የተገኘ ባቄላ፣ አተር እና ቦሎቄ በመጠቀም ስድስት ዓይነት የታሸጉ ምግቦችን በሀገር ውስጥ ማምረት መጀመሩን ኩባንያዉ በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል፡፡

ኩባንያዉ ከውጭ ገበያዎች ወደ ሀገር የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት ለገበያ ማቅረቡን ነዉ ያሳወቀዉ፡፡

እነዚህ የታሸጉ የባቄላ እና የቦሎቄ ምርቶች፤ቀይ ቦሎቄ፣ነጭ ቦሎቄ፣ጥቁር ቦሎቄ፣ ፉል፣አተር እና ጣፋጭ በቆሎን ያካተቱ ናቸዉ፡፡

‹‹በኢትዮጵያ የተመረተ›› የሚል ምልክትን ይዘዉ ወደ ገበያዉ የሚገቡት እነዚህ የጥራጥሬ ምግቦች ለሀገር ውስጥ ገበያ ብቻ ሳይሆን በቅርቡ ዱባይን ጨምሮ ወደ ዓለም አቀፍ ገበያዎችም የሚላኩ ይሆናል ተብሏል።

የዳቺ ፉድ ኢንዱስትሪ ቺፍ ኮሜርሻል ኦፊሰር አቶ ቢንያም ዮሐንስ፤ ለብዙ ዓመታት ጥሬ ባቄላ ልከን የታሸጉ ምርቶችን እንገዛ ነበር ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በዚህ ኢንቨስትመንት ገበሬዎች ፣ሠራተኞችና አምራቾች ከእርሻ እስከ ዓለም አቀፍ መደብሮች ድረስ የእሴት ሰንሰለቱ አካል ሆነዋል ብለዋል፡፡

ኩባንያው የገበያ ፍላጎት እየጨመረ ሲሄድ የምርት አቅምን ለማሳደግና ከገበሬዎች የሚሰበሰብ ምርትን ለማስፋፋት ዕቅድ እንዳለዉም አንስተዋል፡፡

ኩባንያው ከ36 በላይ ምርቶችን የሚያቀርብ ሲሆን፤ በቅርብ ጊዜ የምርቶቹን ቁጥር ከ100 በላይ ለማድረስ እየሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡

እስከዳር ግርማ

ጥር 05/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *