ፈረንሳይ የትራምፕን ንግግር “የፈጠራ ወሬ” ስትል አጣጣለች

በአሜሪካና በፈረንሳይ መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ፍጥጫ ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋግሯል።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ፈረንሳይን አስገድጄ የመድሃኒት ዋጋ አስጨምሬያለሁ” ሲሉ የተናገሩትን ንግግር፤ ፓሪስ “ሀሰተኛ ወሬ” ስትል አስተባብላለች።

በዳቮስ የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ንግግር ያደረጉት ዶናልድ ትራምፕ፤ “በፈረንሳይ ምርቶች ላይ ከፍተኛ ቀረጥ እጥላለሁ ብዬ በመዛቴ ፕሬዝዳንት ማክሮን እጅ ሰጥተዋል” ብለዋል።

ትራምፕ አክለውም፥ ማክሮን በፍርሃት “እሺ ዶናልድ፤ አደርገዋለሁ” እንዳሏቸው ለታዳሚው በፌዝ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ትራምፕ ራሳቸው “Fake News” ሲሉ የሚታዩበትን ተንቀሳቃሽ ምስል በመጠቀም ፈጣን ምላሽ ሰጥቷል።

“ማክሮን የመድሃኒት ዋጋ አልጨመሩም፤ ሊጨምሩም አይችሉም” ያለው መግለጫው፤ በፈረንሳይ የመድሃኒት ዋጋ የሚወሰነው በህግ እንጂ በፕሬዝዳንቱ ፍላጎት እንዳልሆነ ገልጿል።

ይህ ፍጥጫ የተባባሰው ትራምፕ “ግሪንላንድን መግዛት እፈልጋለሁ” የሚል ፍላጎት ካሳዩ እና በአውሮፓ ምርቶች ላይ የቀረጥ ዛቻ ካሰሙ በኋላ ነው።

ማክሮን በበኩላቸው አውሮፓ ለ”ጉልበተኞች” አትሰጥም በማለት የአጸፋ እርምጃ እንደሚወስዱ አስታውቀዋል።

የፈረንሳይ መንግስት የትራምፕን አስተዳደር መረጃዎች ለመሞገት ልዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ እስከመክፈት ደርሷል።

ልዑል ወልዴ

ጥር 14/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *