ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት መስሪያቤታቸው የስድስት ወራት የስራ ግምገማውን በነቀምቴ ከተማ እያደረገ ባለበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ነው።
ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) በንግግራቸው “የህዳሴ ግድብ ዛሬ በአለም መድረክ በትልልቅ የዓለማችን ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች ዘንድ አጀንዳ መሆን የቻለው በስኬት ማጠናነቅ በመቻላችን ነው ” ብለዋል።
በኢትዮጲያዊያን ህዝብ የገንዘብ፣የጉልበትእና የሀሳብ ጠንካራ ድጋፍ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ( ዶ/ር ) ቆራጥ ዉሳኔ እና አመራር ሰጪነት መጠናቀቁ እና ስራ ላይ መዋሉ ዛሬ የአለም ትልቁ አነጋጋሪ አጀንዳ እንዲሆን ምክንያት ሆኗል ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ትላንት አድርገውት በነበረው ንግግር የታላቁ ህዳሴ ግድብን ከዓለም ግዙፍ ግድቦች አንዱ እንደሆነ መጥቀሳቸው የሚታወስ ነው።
ያይኔ አበባ ሻምበል
ጥር 14/2018 ዓ.ም
