ኤጀንሲዉ በስድስት ወራት ዉስጥ 12 ሺህ 16 ሞት መመዝገቡን አስታዉቋል፡፡
3 ሺህ 1መቶ 41 በወቅታዊ፣2 ሺህ6መቶ35 የሚሆኑት በአንድ ዓመት ውስጥ ተከስተው የተመዘገቡ እንዲሁም 6ሺህ2መቶ40 ደግሞ የጊዜ ገደቡ ባለፈ የተመዘገበ ኩነት መሆናቸዉ ተነግሯል፡፡
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ፤ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ ስድስት ወራት የተከናወኑ ዋና ዋና አፈፃፀሞችን መገምገሙን አስታዉቀዋል።
ሌላዉ 1ቶ82 ጉዲፈቻ ምዝገባ የተከናወነ ሲሆን፤ 99 በወቅታዊ፣51 የጊዜ ገደቡ ባለፈ፣እንዲሁም 19 በዘገየ የተመዘገቡ መሆናቸዉን ገልጸዋል፡፡
በ 6 ወር አፈፃፀም 2መቶ36 ሺህ8መቶ74 ልደት ምዝገባ የተደረገ ሲሆን፤ 41 ሺህ1መቶ94 ህፃናት እንደተወለዱ የተመዘገቡ ናቸዉ፡፡
13 ሺህ 9መቶ74 ህፃናት በተወለዱ በ90 ቀናት እንዲሁም 1መቶ1 ሺህ 5መቶ19 ህፃናት ደግሞ ትምህርት ቤቶች ላይ በተደረገ ንቅናቄ የተመዘገቡ መሆናቸዉ ገልፀዋል።
ይሄም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ21 በመቶ እድገት ማሳየቱ ተገልጿል፡፡
ሊዲያ ደሳለኝ
ጥር 15/2018 ዓ.ም
