ኢትዮጵያ በዓለምአቀፍና አህጉር ዓቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ ተወዳዳሪ እንድትሆን ማድረግ የሚቻለው ለጥራት ቅድሚያ የሚሰጡ ድርጅቶችን በመፍጠር ነው ተባለ

ኢትዮጵያ በዓለማቀፍና አህጉር ዓቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ ተወዳዳሪ እንድትሆን ማድረግ የሚቻለው ለጥራት ቅድሚያ የሚሰጡ ድርጅቶችን በመፍጠር ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ ይህን የተናገሩት በቦርድ ሰብሳቢነት የሚመሩት የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ያዘጋጀው አራተኛው የልህቀት መድረክ ሐሙስ ጥር 14 ቀን 2018 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደበት ወቅት ነው።

በመድረኩ የኢትዮጵያ ተወዳዳሪነት የሚወሰነው በተቋማቱ ተወዳዳሪነት እንደሆነ የገለፁት ዶ/ር ሳሙኤል፤ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ብትሆን፣ የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና አባልም ብትሆን፣ በአገር ደረጃም ከውጭ የሚመጡ ዕቃዎችን ለመተካት ብትተጋም፣ ተቋማቱ ጠንካራ ካልሆኑ በማበረታቻዎች ብቻ ስኬት ማምጣት አይቻልም ብለዋል።

ይህን በማሳካት በአፍሪካ ደረጃ ተወዳደሮ ለማሸነፍ፤እንዲሁም በዓለማቀፍ ደረጃ ቆሞ ለመቀጠል ለጥራት ቅድሚያ የሚሰጡ ድርጅቶችን መፍጠር ያስፈልጋል ሲሉም ነው የተናገሩት።

የኢትዮጵያ ተወዳዳሪነት በተቋማቱ ተወዳዳሪነት ይወሰናል ያሉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እና የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢው ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ናቸዉ።

በመድረኩ በአገር ዓቀፍ የጥራት ሽልማት ውድድር ተሳትፈው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ የመንግሥትና የግል ተቋማት ለስኬት ያበቋቸውን ምርጥ ተሞክሮዎች ለሌሎች ድርጅቶች አካፍለዋል።

አዲስአለም አበበ

ጥር 15/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *