የኤሌክትሪክ ሀይል ተደራሽ ባልሆነባቸዉ አካባቢዎች የታዳሽ ሀይል ስርዓቶችን ለመተግበር የሚያስችል ስምምነት ተደረገ

በዛሬዉ ዕለት የቻይናዉ ሳዉዘር ፓዉር ግሪድ ቴክኖሎጂ እና ኤንዳ ኤሌክትሮ ፓወር ግሩኘ ለአራት አመት የሚቆይ የዉል ስምምነት ተፈራርመዋል።

ሳዉዘር ፓዉር ግሪድ ቴክኖሎጂ የተሰኘዉ የቻይና ተቋም ግሪን ቴክኖሎጂ ወይም ሀይልን ከሀይድሮ ኤሌክትሪክ ሀይል ብቻ ሳይሆን የአረንጓዴ ቴክኖሎጂን ለማቅረብ እንደሚችል ተነግሯል።

ኤንዳ ኤሌክትሮኒክስ ከቻይና የሚመጡትን የአረንጓዴ የቴክኖሎጂ አይነቶች ኢትዮጵያውያን የሰዉ ሀይል በማሰልጠን ቴክኖሎጂዉን ሀገር ዉስጥ የማስቀረት አላማ ያለዉ መሆኑን የነገሩን የኤንዳ ፓወር የኮምኒኬሽን ሀላፊ አቶ ሀምዴ ኢብራሂም ናቸዉ።

አቶ ሀምዴ የስምምነቱ አጋርነት ዘመናዊ የሀይል ማከፋፈል እና ማከማቻ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሀገር ዉስጥ ማስገባትን አላማ ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ከመንግሥት ጋር በመቀራረብ የሚሰራ ኘሮጀክት መሆኑን ጠቅሰዉ ለጊዜው ግን ቴክኖሎጂዉን አጥንቶ ማሰልጠን÷ ቴክኖሎጂዉ ሀገር ዉስጥ መትከል ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

የቻይናዉ ሳዉዘርን ፓወር ግሪድ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ተወካይ ዣኦ ዚዪ ቴክኖሎጂዎቹ በተለይም ኢትዮጵያ ከጀመረችዉ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ሽግግር መመጣጠን የሚችል ነዉ ብለዋል።

በፊርማ ስምምነቱ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ÷ ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወክለዉ የተገኙት አምባሳደር ደዋኖ ከድር እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተደርጓል።

ቁምነገር አየለ

ጥር 18/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *