የህንድ ማሃራሽትራ ግዛት ምክትል ሚኒስትር በአውሮፕላን አደጋ ህይወታቸው አለፈ

የህንድ ባለጸጋ ግዛት የሆነችው የማሃራሽትራ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አጂት ፓዋር፣ ረቡዕ ዕለት በተከሰተ የቻርተር አውሮፕላን አደጋ ከሌሎች አራት ሰዎች ጋር መሞታቸውን የሀገሪቱዋ የአቪዬሽን ተቆጣጣሪ ገልፁዋል።

ከታዋቂ የፖለቲካ ቤተሰብ የተወለዱት ፓዋር፣ አደጋው የደረሰው በአካባቢያዊ ምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ ወደ ትውልድ አካባቢያቸው በመጓዝ ላይ ሳሉ እንደነበር መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

እንደ ሲቪል አቪዬሽን ዋና ዳይሬክቶሬት መግለጫ ከሆነ፣ በ ቪ.ኤስ.አር ቬንቸርስ (VSR Ventures) በሚተዳደረው ሊርጄት 45 አውሮፕላን ውስጥ ሁለት የፓዋር ረዳቶች እና ሁለት የአውሮፕላኑ ሰራተኞች ይገኙ ነበር።

መስሪያ ቤቱ በመጀመሪያው መግለጫው “በአውሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩት መካከል የተረፈ ሰው የለም” ብሏል።

የ ቪ.ኤስ.አር ቬንቸርስ ዳይሬክተር ቪኬ ሲንግ ለ “ኢንዲያ ቱዴይ” እንደተናገሩት፣ አውሮፕላኑ የወደቀው ወደ ባራማቲ ከተማ ለመድረስ ሲቃረብ ቢሆንም የአደጋው መንስኤ ግን እስካሁን አልታወቀም። ዳይሬክተሩ አክለውም “አውሮፕላኑ 100% አስተማማኝ ነበር፤ የአውሮፕላኑ ሰራተኞችም በቂ ልምድ ያላቸው ነበሩ” ብለዋል።

በቪዲዮ ምስሎች የአውሮፕላኑ ፍርስራሽ በሜዳ ላይ ተበታትኖ ጭስ ሲወጣው ታይቱዋል ፤ አንድ ስሙ ያልተጠቀሰ የአይን እማኝ ለኤ.ኤን.አይ (ANI) የዜና ወኪል ሲናገር “መጀመሪያ አውሮፕላኑ በእሳት ተያያዘ፣ ከዚያም አራት ወይም አምስት ጊዜ ተከታታይ ፍንዳታዎች ተሰሙ” ብሏል፤እሳቱ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ማንንም ማዳን እንዳልተቻለም ሲልም አክሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ በኤክስ (X) ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የፓዋር ሞት “አስደንጋጭ እና የሚያሳዝን” ነው ብለዋ ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ሀና ሰይፉ

ጥር 20/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *