ከንቲባዋ ይህንን ያሉት አስተዳደራቸው የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት አፈፃፀም ግምገማ ላይ ባደረጉት የማጠቃላያ ንግግር ነው፡፡
ከንቲባ አዳነች ” የምርጫ አመት ስለሆነ የማንችለውን ቃል አንገባም ፡፡የሰራነውን ህዝባችን በሚገባ ስላሳየነው እና እየተጠቀመበት ስለሆነ ካቀድነው ውጪ አዳዲስ ጫናዎችን አንፈጥርም ” ብለዋል፡፡
” የምንመራው በእቅድ የምንሰራውም በታቀደ በጀት ስለሆነ ፈጣን ምላሽ የሚሹ ስራዎች ሲኖሩ ፈትሹ ወደ ተግባር መግባት ፤ የተጀመሩትንም ጥንቅቅ አድርጎ እና ጥራታቸውን ጠብቁ መስራት እና ለአገልግሎት የማዋል ስራ ተጠናክሩ ይቀጥላል” ብለዋል ፡፡
በተሰሩት ስራዎች መኩራራት ወደኋላ ይጉትታል ያሉት ወ/ሮ አዳነች እርካታ ፤ መዘናጋት የብልጽግና አመራር ባህሪ አይደለም ህዝቡ የሚጠብቀው እና እኛም ያለብንን ሀላፊነት መወጣት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ጥር 20/2018 ዓ.ም
