ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባሳለፍናቸው 3 ዓመታት ውስጥ የኢትዮጲያ ኢንዱስትሪዎች ከፍተኛ መነቃቃትን እንዳሳዩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 10ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ባለበት ወቅት ተናግረዋል፡፡
በሀገራችን ውስጥ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች በስድስት ወራት ውስጥ ብቻ የኢነርጂ አጠቃቀማቸውን በ 16 በመቶ አሳድገዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ 2.3 ሚሊየን የሚያህሉ ቢዝነሶች በሀገሪቷ ውስጥ በስራ ላይ እንደሚገኙ አክለዋል፡፡
ከነዚህ አምራቾች መካከል 4መቶ13 ሺህ ወይም 17 በመቶዎቹ አምራች ኢንዱስትሪዎች ናቸው ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፉት 6 ወራት ከፍተኛ የኢንዱስትሪ መጠንን ያሳድጋል በሚል ትላልቅ ኢንቨስተሮችን ወደ ሀገር ውስጥ አስገብተናል በዚህም ከፍተኛ የሆነ ለውጥን አስመዝግበናል ብለዋል፡፡
ለማሳያነትም የቬትናሙ ቶዩ የጠቀሱ ሲሆን፤ ወደ ሃገር ውስጥ ገብቶ ስራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ 6.6 ሚሊየን አክስፖርት ማድረጉን አንስተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፈው አመት እና በዘንድሮ አመት ብቻ የኤክስፖርት አቅሙን በዕጥፍ አሳድጓል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ፤ አጠቃላይ ኢንዱስትሪው መነቃቃት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
ሀና ሰይፉ
ጥር 26/2018 ዓ.ም
