በስድስት ወራት ውስጥ 2.6 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሯል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

በ6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዘንድሮው አመት በጠቅላላ ከ 3.3 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ አድል እንደተፈጠረ አስታውቀዋል ፡፡

ለዚህም ምክንያት የጠቀሱት ጠቅላይሚኒስተሩ በከተማ እና በገጠር የሚሰሩ ኮሪደሮች እንዲሁም እየተነቃቁ ያሉ የአገልግሎት ዝርፎች ነው ፡፡

በተጨማሪም ባለፉት ስድስት ወራት የውጭ ሃገር የስራ አድል ከ350 ሺህ ሰው በላይ የውጭ የስራ እድል ማግኘቱን ጠቅላይ ሚኒስተሩ ገልፀዋል ፡፡

በውጭ ሃገር የስራ አድል ካገኙ ዜጎች ውስጥ ከ 7 ሺህ አስከ 10 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች በሙያቸው ብቁ የሆኑ መሆናቸውን ጠቅሰዋል ፡፡

ሌላው ጠቅላይ ሚኒስተሩ ያነሱት ሃገር ውስጥ ተቀምጠው ለውጭ ሃገር ድርጂቶች ስለሚሰሩ ዜጎች ሲሆን ባለፉት ስድስት ወራት ከ 20 ሺህ በላይ ዜጎች ስራ ላይ እንደተሰማሩ አስታውቀዋል፡፡

አቤል እስጤፋኖስ

ጥር 26/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *