የባንክ ዘርፉን ከመቆጣጠር ወደ ነጻ ገበያ መሸጋገሩ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ መረጋጋት ቁልፍ ሚና አለው -ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ

በባንኮች መካከል ያለው የገንዘብ ግብይት ከብሄራዊ ባንክ ውጭ መካሄድ መቻሉ እና ባንኮች በራሳቸው አማራጭ እንዲጠቀሙ መደረጉ በርካታ ለውጦችን እንዳመጣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ለምክር ቤት አባላት ምላሽ እየሰጡ ባሉበት ወቅት አብራርተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገራችን ባንኮች ባሳለፍናቸው 6 ወራት ውስጥ ከ 6 ትሪሊየን ያላነሰ ገንዘብ ተሻሽጠዋል ያሉ ሲሆን፤ የገንዘብ አቅርቦት መጠንም በ10 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን ገልጸዋል፡፡

ቁጠባ ከ44 በመቶ በላይ ጭማሪ አሳይቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ፤ ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር የተሰበሰበ ብድር በ68 በመቶ ጨምሯል ብለዋል፡፡

የቀረበ ብድር ደግሞ ወደ 1መቶ23 በመቶ አድጓል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ከውጤቱ ውስጥ 90 በመቶ የሚሆነው ወደ ግል ሴክተሩ የሄደ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ሀና ሰይፉ

ጥር 26/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *