በሆነ ጊዜ ማርጀትም ሆነ በጊዜ መድከም ቢኖርም ቀይ ባህርና ኢትዮጵያ እንደዚህ ናቸዉ መቼም አይነጣጠሉም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ።
ኢትዮጵያ የባህር በር አያስፈልጋትም ብሎ የሚያምን ሰዉ አንድ ተፈጥሮዉ ህግ የሳተ ሰዉ መሆን አለበት ብለዋል።
ከምጽዋ ጫፍ እስከ ሞቃድሾ ጫፍ 5 ሺ ኪሎ ሜትር ነዉ፤ ከዚህ ዉስጥ 20 ሚሊየን ህዝብ ያላት ሱማሊያ ሌላዉን ጅቡቲ እና ኤርትራ በድምሩ 25 ሺዉን መያዛቸዉን ገልጸዉ፤1መቶ 30 ሚሊየን ህዝብ ያላት ኢትዮጵያ ግን የጠየቀችዉ 50 ኪሎ ሜትር መሆኑን አንስተዋል፡፡
ይህ ፍትህ ካልሆነ አለም ላይ ፍትህ የለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ፤ የጠየቅነዉ ገድለን ወይም ቀምተን ሳይሆን በህጉ መሠረት ነዉ ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግስትን የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለፓርላማዉ ባቀረቡበት ወቅት ነዉ ይህን የተናገሩት።
የኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ቀይ ባህርን ለመጠየቅ ሰዉ ልግደል አላለም፤ በሰላም ነገሩን እንፍታዉ ነዉ ያለዉ ይሄን መቀበል ደግም የጊዜ ጉዳይ እንጅ የግድ ይሆናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 10ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት አካሂዷል፡፡
ሊዲያ ደሳለኝ
ጥር 26/2018 ዓ.ም
