የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዛሬው ዕለት ያካሄደውን የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት ይፋ አድርጓል። By Ethio AdminFebruary 3, 2026February 3, 2026የሀገር ውስጥ ዜና ለጨረታ 70 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር መቅረቡንና በሒደቱ 19 ባንኮች መሳተፋቸውን ጠቅሶ÷ 8 ባንኮች በጨረታው ማሸነፋቸውን ገልጿል። በምንዛሪ ጨረታው አንድ የአሜሪካ ዶላር ዋጋ በአማካኝ 155 ነጥብ 0506 ብር ሆኖ መመዝገቡ ተገልጿል፡፡ ብሔራዊ ባንክ ቀድሞ በወጣው መርሐ ግብር መሰረት ተመሳሳይ ጨረታ በቀጣይ እንደሚያካሂድም አስታውቋል፡፡ ጥር 26/2018 ዓ.ም