መቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ለየካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም አቅዶት የነበረው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር መራዘሙን አስታወቀ።

ማዕከሉ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከተው፤ ፕሮግራሙ ወደ መጋቢት 6 ቀን 2018 ዓ.ም ተዛውሯል።

የማዕከሉ መሥራች ዶ/ር ቢኒያም በለጠ በመግለጫው ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤ በአሁኑ ወቅት ከ9 ሺህ በላይ ወገኖችን እየረዳ የሚገኘው ማዕከሉ፣ በመላው ሀገሪቱ የሚከናወኑ የሰብዓዊ ድጋፍ ስራዎችን ለማጠናከር ይህ መርሃ-ግብር ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

ዶ/ር ቢኒያም ለመላው ኢትዮጵያውያን ጥሪ ካቀረቡ በኋላ እስካሁን ለተደረገው ተከታታይ ድጋፍና ተሳትፎ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ይህ የገቢ ማሰባሰቢያ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ቅርንጫፎችን አቅም ለማሳደግና ተጨማሪ ዜጎችን ከጎዳና ለማንሳት የሚደረገው ጥረት አካል መሆኑም ተመላክቷል።

አቤል እስጢፋኖስ

ጥር 29/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *