በዛሬዉ ዕለት ብልፅግና ፓርቲ ለሰባተኛዉ አገር አቀፍ ምርጫ የመወዳደሪያ የምርጫ ምልክቱንና ማኒፌስቶውን በዋና የፓርቲዉ ፅህፈት ቤት ይፋ አድርጓል።
የፓርቲዉ የምርጫ ቅስቀሳ ሃደትም በይፋ መጀመሩን ዛሬ እየተካሄደ ባለዉ መርሃግብር ላይ ተነግሯል።
በመድረኩ ለሰባተኛዉ ሀገራዊ ምርጫ የመወዳደሪያ ምልክቱን ተምሳሌት አስመልክቶ በተሰጠዉ ማብራሪያ ምልክቱ የመደመር፣ የትብብርና እና የአንድነት ተምሳሌት ነዉ ሲል ፓርቲዉ ገልጿል።
የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤት ሀላፊ አደም ፋራህ፤ ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር መትጋት የምርጫ ማኒፌስቶዉ እሳቤ ነዉ ሲሉ ገልፀዋል።
አቶ አደም ፋራህ ፓርቲዉ በሚቀጥሉት አመታት ሊፈታቸዉ ከያዛቸዉ ችግሮች መካከል ግጭቶችን በዘላቂነት መፍታት፣ የሽግግር ፍትህ ስርአትን መዘርጋት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት መሆኑን በመድረኩ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የባህር በር ልታገኝበት የምትችልበትን ሁኔታ መፍጠር እና ማመቻቸት ከፓርቲዉ ዕቅዶች ዉስጥ ይገኙበታል ሲሉ ሀላፊዉ ገልፀዋል።
“ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ” ሲል ያስተዋወቀዉ የብልፅግና ፓርቲ ማኒፌስቶ፤ ምርጫዉን በሰላማዊ መንገድ ለማከናወን የሚቻልበት አግባብ ይፈጥራል ሲሉ በዛሬዉ ዕለት በተካሄደዉ የፓርቲዉ የምርጫ ምልክት እና ማኒፌስቶ ማስተዋወቂያ መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ አደም ፋራህ ተናግረዋል።
ቁምነገር አየለ
የካቲት 03/2018 ዓ.ም
