ዝግ የሚደረጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ

39ኛውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ አስመልክቶ የተሽከርካሪ ፍሰቱን ለማሳለጥና ከእንግዶች አቀባበል ጋር በተያያዘ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።

ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ብራስ እንዲሁም ከቦሌ መድኃኔዓለም በአትላስ ወደ ቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ በመሪዎቹ ጉባኤ ምክንያት ከዛሬ የካቲት 4 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚደረግ ይሆናል።

በተጨማሪም በሌሎች እንግዶች በሚያርፉባቸው ዋና ዋና አደባባዮችና የአጀብ መስመሮች አሽከርካሪዎች ቅድሚያ በመስጠትና የትራፊክ ፖሊስ አባላትን ትዕዛዝ በማክበር የተለመደ ቀና ትብብራቸውን እንዲያደርጉ፤ በተጠቀሱት ቦታዎች ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪዎችን ማቆም የተከለከለ መሆኑንም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ እያስታወቋል።

የካቲት 04/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *