የባንግላዲሽ ነዋሪዎች ለቀጣዩ መሪ እና ለአዲሱ መንግስት ምስረታ ብቻ ሳይሆን ለአገሪቱ የፖለቲካ የወደፊት እጣ ፈንታም ድምጽ ይሰጣሉ ነው የተባለው።
ዛሬ የሚደረገው ምርጫ የጀነራል ዜድን ኃይል እንደሚፈትሽ ተነግሯል።
ጄኔራሉ አሁን ትልቅ የምርጫ ቡድን በመኖሩ ይህ ምርጫ እውነተኛ ለውጥ ያመጣል ብለው እንደሚያምኑ ገልፀዋል።
መራጮች አዲስ ሕግና መንግሥታዊ አካላትን መፍጠርን ጨምሮ በአራት ዋና ዋና ማሻሻያዎች ላይ መወሰን የሚችሉበት እድል ይኖራቸዋል ተብሏል።
በሌላ በኩል የጠቅላይ ሚኒስትሮችን የስልጣን ጊዜ ገደብ እና የፕሬዚዳንታዊ ስልጣን መጨመርን ጨምሮ የ30 ቻርተር ማሻሻያዎችን አፈፃፀም የመታዘብ እድል ያገኛሉ ነው የተባለው።
በምርጫው ወቅት የተገኘው አብላጫ ድምፅ ማሻሻያውን የሚደግፍ ከሆነ በመጀመሪያ ጉባኤው በ1መቶ80 የሥራ ቀናት ውስጥ የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ምክር ቤት ይቋቋማል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።
ሊዲያ ደሳለኝ
የካቲት 05/2018 ዓ.ም
