በአመት ውስጥ ከ3.6 ሚሊየን በላይ ህጻናት እና ከ9 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ልጃገረዶች ከተለያዩ በሽታዎች መከላከል የሚችል ክትባት እንዲያገኙ መደረጉን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በኢትዮጵያ ህጻናት ለተለያዩ በሽታዎች እንዳይጋለጡ ለመጠበቅ እስከ አምስት አመት ድረስ ያሉ ህጻናት ክትባት እንዳገኙ እና ሴት ልጃገረዶች በካንሰር በሽታ እንዳይጠቁ ለመከላከል ክትባት እንዲያገኙ ለማድረግ ጤና ሚኒስቴር በስፋት እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
በጤና ሚኒስቴር የክትባት አገልግሎት አማካሪ አቶ ሽፈራው ጌታቸው፥ በአንድ አመት ውስጥ 3.6 ሚሊየን ህጻናትን በክትባት ተደራሽ ማድረግ እንደቻሉ ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ሴት ልጃገረዶች በማህጸን በር ካንሰር በሽታ እንዳይጠቁ ለማድረግ ወይንም ለመከላከል ከ9 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ተደራሽ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።
ሀና ሰይፉ
የካቲት 06/2018 ዓ.ም
