የጅማ አይን ባንክ በለጋሾች ዕጥረት ምክንያት ከ5ሺህ በላይ ታካሚዎች ወረፋ እየጠበቁ መሆኑን አስታወቀ

አንድ ሰው ሲሞት ለሁለት ሰዎች ብርሃን መስጠት እንደሚችል ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡

የጅማ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ማዕከል የአይን ብሌን ንቅለ ተከላ ለማድረግ የሚያስችል የሰለጠነ የሰው ኃይል እና ቴክኖሎጂ ቢኖረውም፤ በለጋሾች እጥረት ምክንያት ከ5 ሺህ በላይ ታካሚዎች ወረፋ ለመጠበቅ መገደዳቸውን አስታወቀ፡፡

የህክምና ማዕከሉ ክሊኒካል ዳይሬክተር ዶ/ር ሁንዴ አህመድ፥የአይን ብሌን ንቅለ ተከላ አገልግሎቱ በክልል ደረጃ ብቸኛው ቢሆንም፣ በማህበረሰቡ ዘንድ ያለው የግንዛቤ እጥረት ለስራው እንቅፋት ሆኗል ብለዋል።

አንድ ሰው ሲያልፍ የሁለት ሰዎች አይን ማዳን ይችላል ያሉት ዶክተሩ፥የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ህብረተሰቡ ከህልፈት በኋላ የአይን ብሌን እንዲለግስ በማስተማር በኩል እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ በካንሰር ህክምና ላይም ታካሚዎች ህመሙ ደረጃው ከፍ ካለ በኋላ ወደ ጤና ተቋም እየመጡ መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊው፥ የህክምናው ውጤታማነት ከፍ እንዲል ቅድመ ምርመራ ባህል እንዲዳብር የማህበረሰብ አቀፍ የጤና ትምህርት በስፋት መስጠት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

የካቲት 06/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *