አፍሪካ የመጪው ዘመን የጣዕም ልኬት ትሆናለች – ማርከስ ሳሙኤልሰን

ዝነኛው ኢትዮጵያዊ ሼፍ ማርከስ ሳሙኤልሰን
ከሲ.ኤን.ኤኗ ላሪ ማዶዎ ጋር ባደረገው ቆይታ “የድንቅ ምግቦች ባለቤት መሆናችንን እናውቃለን” ብሏል። “ምግባችን ጣፋጭ እንዲሁም ከመንፈሳችን እና ታሪካችን ጋር የተሳሰረ ነው። ታዲያ መመዘኛው ከሌላ ቦታ እንዲመጣ የሚጠበቀው ለምንድን ነው?” የሚል መከራከሪያ ያነሳል።

ሳሙኤልሰን የአፍሪካ ምግቦችን የነጠላ ታሪክ የመለወጥ ተስፋ ሰንቋል። አፍሪካ በዓለምዓቀፍ የምግብ ባህል የምትገለጽበትን መንገድ በአዲስ መንገድ ለመለወጥም ተነሳሰቷል።

“አፍሪካ አህጉር ናት። የሴኔጋላውያን ምግብ ከኢትዮጵያውያን ይለያል።

የሞሮኮ ምግብ ከደቡብ አፍሪካውያን ምግብ የተለየ ነው። አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ስለ አፍሪካ የሚያወሩት በደፈናው እንደ አንድ በመቁጠር ነው።

እንዲህ ዓይነቱ ልዩነትን ያልተረዳ ልሙጥ ፍረጃ የአፍሪካውያን ድንቅ የምግብ ዝግጅት ጥበብ የሚገባውን እውቅና ሳያገኝ እንዲቆይ አስገድዷል ብሎ ያምናል።

እውቅና ሳያገኝ የቆየው ስላልነበረ ሳይሆን በራሱ መንገድ ስላልተገለጸ ነው ባይ ነው።

የአፍሪካ የምግብ ባህል ጥንቅቅ ባለ የምግብ ዝግጅት ሂደት ውስጥ ያሉ ነገሮችን ሁሉ ይዟል። ቴክኒኮቹ ፣ ታሪክ ነገራው፣ ስርዓቱ ፣ ከማህበረሰቡ ጋር ያለው ትስስር ይንጸባረቅበታል። መልከዓምድር፣ የአየር ጠባይ እና ታሪክ የምግቦቹን ልዩ ባህሪይ እንደሚቀርጽ ያምናል።

ሳሙኤልሰን የአፍሪካ ምግብ ስለሚያመራበት መንገድ ሲናገር ጥሩ ማሳያ አድርጎ የሚያቀርበው ሙዚቃን ነው።  አፍሮቢትስ፣ አማፒያኖ እና ሌሎች የሙዚቃ ዘውጎች በዓለም ተቀባይነት ከማግኝታቸው በፊት ታማኝ አድማጭ ያገኙት በአህጉሪቱ ነው” ብሏል።

የአፍሪካ ባህል የዓለም ፋሽን፣ ሙዚቃ እና ስነ ጥበብ ላይ ተጽዕኖ ማሳረፉን ቀጥሏል። ቀጣዩ ስነ ምግብ ነው።

አቤል ጀቤሳ

የካቲት 06/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *