ትናንት በስፔን ባርሴሎና በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር ሐጎስ ገብረሕይወት አሸንፏል፡፡

አትሌቱ ከፍተኛ ብቃቱን ባሳየበት በዚህ ውድድር ርቀቱን ለመጨረስ የፈጀበት ጊዜ 58:05 ነው፡፡

ይህም በርቀቱ የ2026 ፈጣኑ ሰዓት ሆኖ ተመዝግቦለታል፡፡

2ኛ የወጣውን ስዊዘርላንዳዊውን ዶሚኒክ ሎባሉንም (59:25) ከአንድ ደቂቃ በላይ ቀድሞ ነው የገባው።

ፈረንሳዊው ኢማኑኤል ሩዶልፍ (59፡37) ሶስተኛ ሲወጣ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ሀጎስ እዮብ (59፡42) አምስተኛ በመሆን ውድድሩን ጨርሷል፡፡

በሴቶቹ ምድብ ኬንያዊቷ ሎይስ ቼሙኑንግ 1:04:01 በሆነ ጊዜ በቀዳሚነት በመግባት አዲስ የቦታውን ክብረወሰን አሻሽላለች።

አሜሪካዊቷ ወይኒ ቀላቲ (1፡06.04) ሁለተኛ፤ ኢትዮጵያዊቷ ዲኒያ ከድር (1፡06.28) ሶስተኛ ወጥተዋል፡፡

ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት ነፃነት ደስታ ደግሞ (1፡08.10) በሆነ ጊዜ በሰባተኛነት ውድድሯን አጠናቅቃለች፡፡

ምስጋናው ታደሰ
የካቲት 9/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *