አትሌት ሹራ ቂጣታ እና አስራር ሀይረዲን እስከ መጨረሻዋ መስመር ድረስ ያደረጉት ትንቅንቅ የበርካቶችን ቀልብ የሳበ ነበር፡፡
ሁለቱም 2፡03.59 በሆነ እኩል ሰዓት ቢገቡም በፎቶ ፊኒሺንግ ግን ሹራ አሸናፊ ለመሆን ችሏል፡፡ ደጀኔ ሃይሉ ደግሞ በ2፡04.15 በሶስተኛነት ውድድሩን አጠናቅቋል፡፡
በዚሁ ምድብ ካፒታል ደገፋ፣ ፅዳት አበጀ፣ ፈይሳ ሙሉ እና ልመንህ ጌታቸው ከ5ኛ እስከ 8ኛ ወጥተዋል፡፡
ሎተሪ ወ/ጊዮርጊስ እና እምባይ ጎይቶም 10ኛ እና 11ኛ ሲወጡ ሀብታሙ ብርሌው 17ኛ እንዲሁም ነጋሳ ሌሊሳ 23ኛ ሆነው ውድድራቸውን አጠናቅቀዋል፡፡
በዚሁ የሲቪያ ማራቶን የሴቶች ምድብ ፊንላንዳዊቷ አሊሳ ቫይኒዮ (2፡20.39) ኬንያዊቷን ቢያትሪስ ጄፕቼርቺርን (2፡21.56) አስከትላ በመግባት አሸንፋለች፡፡
ኢትዮጵያዊቷ ሙላት ተክሌ 2፡22.03 በሆነ ሰዓት 3ኛ ወጥታለች፡፡
ኡርጌ ዲሮ እና አዳወርቅ አበርታ ደግሞ 11ኛ እና 12ኛ ሆነው ውድድሩን ፈፅመዋል፡፡
ምስጋናው ታደሰ
የካቲት 9/2018 ዓ.ም
