ጣሊያን በአየር ንብረት አደጋ ለተጠቁ አገራት የዕዳ ክፍያ እንዲያቆዩ እንደምትፈቅድ ገለጸች

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ፤ ጣሊያን እና አፍሪካውያን አጋሮቿ የቅርብ ጊዜ ውይይታቸውን በአህጉሪቱ የዕዳ ጫና ላይ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

ጣሊያን አገራት በከባድ የአየር ንብረት አደጋዎች በሚጠቁበት ጊዜ የዕዳ ክፍያቸውን እንዲያቆዩ ዕድል እንደምትሰጥ ተናግረዋል።

ሜሎኒ በአዲስ አበባ በተካሄደው ሁለተኛው የጣሊያን-አፍሪካ ስብሰባ ማጠቃለያ ላይ ፤ ዛሬም በድጋሚ ለአፍሪካ ቁልፍ በሆነው የዕዳ ጉዳይ ላይ ትኩረት አድርገናል ብለዋል።

ለጋራ የልማት ፕሮጀክቶች የሚውል ሰፊ የዕዳ ሽግግር ተነሳሽነት ጀምረናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሯ፤ ከዚህ በተጨማሪም በከባድ የአየር ንብረት አደጋዎች ለተጠቁ አገራት የዕዳ ክፍያን ለጊዜው የሚያቆዩ አንቀጾችን እያስተዋወቅን ነው ብለዋል።

ሜሎኒ የታቀደው የዕዳ ማቆያ ሥርዓት እንዴት እንደሚሠራ ወይም የትኞቹ አገራት ተጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚችሉ ዝርዝር መረጃ አልሰጡም።

ጣሊያን ከአፍሪካ አገራት ጋር የምታደርገውን ትብብር የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ ማዕዘን ያደረገችው ሲሆን፤ በተለይም ‹‹የማቲ ዕቅድ›› በተባለው ፕሮግራሟ አማካኝነት በኢነርጂ፣ በግብርና እና በመሠረተ ልማት ዘርፎች የረጅም ጊዜ አጋርነትን ለመገንባት ማለሟን ገልጻለች።

እስከዳር ግርማ

የካቲት 09/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *