ቻይና ለካናዳ ዜጎች ያለ ቪዛ የመግባት መብት ሰጠች

የካናዳዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኒ ከቻይና ጋር ያለንን ግንኙነት እያደስን ነው ብለዋል፡፡

በአዲሱ ስትራቴጂካዊ አጋርነታችን መሠረት ቻይና ለካናዳውያን ያለ ቪዛ የመጓዝ ዕድል እየሰጠች ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደገለጸው፤ መደበኛ የፓስፖርት ባለቤት የሆኑ የካናዳ ዜጎች ከዛሬ ጀምሮ ያለ ቪዛ ወደ አገር ውስጥ መግባት ይችላሉ።

ፖሊሲው ለንግድ፣ ለቱሪዝም፣ ለቤተሰብ ጥሪ እና ለትራንዚት እስከ 30 ቀናት ቆይታን ይፈቅዳል።

ቤጂንግ ለካናዳውያን የ30 ቀናት የቪዛ ነፃ ቆይታ መፍቀዷ፣ ከዓመታት ውጥረት በኋላ ግንኙነቱ መሻሻሉን የሚያሳይ ምልክት ተደርጎ ተወስዷል።

የካናዳዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኒ፤ከቻይና ጋር ያለንን ግንኙነት እያደስን ነው። በአዲሱ ስትራቴጂካዊ አጋርነታችን መሠረት ቻይና ለካናዳውያን ከቪዛ ነፃ ጉዞ እየፈቀደች ነው ሲሉ በኤክስ ገጻቸው ላይ የጻፉ ሲሆን፤ ፖሊሲው ግንኙነቱ መሻሻሉን የሚያሳይ ግልጽ ምልክት እንደሆነ ገልጸዋል።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደገለጸው፤መደበኛ የፓስፖርት ባለቤት የሆኑ የካናዳ እና የእንግሊዝ ዜጎች ከዛሬ ጀምሮ ያለ ቪዛ ወደ አገር ውስጥ መግባት ይችላሉ። ይህ ፖሊሲ ለንግድ፣ ለቱሪዝም፣ ለቤተሰብ ጥሪ እና ለትራንዚት እስከ 30 ቀናት ቆይታን ይፈቅዳል ብሏል።

እርምጃው እስከ ታኅሣሥ 31 ቀን 2026 ድረስ ጸንቶ እንደሚቆይም አክሎ ገልጿል።

ይህ ውሳኔ የተላለፈው ካርኒ በጥር ወር ወደ ቤጂንግ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ ሲሆን፤ የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመርም በተለየ ጉብኝታቸው ወቅት ከፕሬዝዳንት ዢ ሺንፒንግ ጋር ስምምነት ላይ ደርሰዋል ነዉ የተባለዉ።

ይህ የቪዛ ነፃ መደረግ ከዓመታት ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት በኋላ የታየ ለውጥ ሲሆን፤ በወቅቱ ቤጂንግ በካናዳውያን ላይ የቪዛ ግዴታን አጥብቃ ከመያዟም በላይ የቻይና የቱሪስት ቡድኖች ወደ ካናዳ እንዳይጓዙ ገድባ ነበር።

ከዚህ ቀደም አብዛኞቹ ካናዳውያን ተጓዦች ረጅም የማመልከቻ ሂደት እና ወደ 1መቶ40 ዶላር የሚጠጋ ክፍያ ይጠበቅባቸው ነበር።

ቻይና ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኋላ ቱሪዝምን እና ዓለም አቀፍ ጉዞን ለማነቃቃት በምታደርገው ጥረት ባለፉት ጥቂት ዓመታት ለበርካታ የምዕራባውያን አገራት የቪዛ ነፃ መብትን አስፋፍታለች።

እስከዳር ግርማ

የካቲት 10/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *