የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የካቲት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ፤ ኮሚሽኑ ያልተከናወኑ ተግባራትን እንዲያጠናቅቅ የሥራ ዘመኑን ለተጨማሪ 8 ወራት ማራዘሙ ይታወሳል።
በዚህም መሠረት ኮሚሽኑ በቀጣዮቹ ስምንት ወራት ውስጥ የሚከተሉትን ስድስት ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት ማቀዱን አስታውቋል፦
የመጀመሪያ ያደረገዉ በትግራይ ክልል የሚደረግ የምክክር ሂደት ነዉ፡፡በክልሉ የሚጠበቀውን የምክክር ሂደት በንቃት ማከናወን፤
እስካሁን የተሰበሰቡ አጀንዳዎችን በየፈርጁ ለይቶ በማዘጋጀትና በመቅረጽ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ፤
ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የሚሆኑ አወያዮችን እና አመቻቾችን መለየትና አስፈላጊውን ስልጠና መስጠት፤
ሁሉንም ድምጾች የሚያስተናግድ፣ አሳታፊና አካታች የሆነ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤን ማካሄድ፤
ከምክክሩ የሚገኙ ውጤቶችን በማጠናቀር የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ማዘጋጀትና አፈጻጸማቸውን መከታተል፤
ሀገር አቀፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን ማስፋትና የዶክመንቴሽን ሥራዎችን በዘመናዊ የዲጂታል ዘዴ ማደራጀት።
ኮሚሽኑ ባለፉት አራት ዓመታት ለተደረገለት ሁለንተናዊ ድጋፍ ምስጋናውን አቅርቦ፤ ቀጣዩ ምዕራፍ ለሀገራዊ መግባባት ወሳኝ በመሆኑ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።
የካቲት 16/2018 ዓ.ም
