የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በዳርፉር ሌላ ከተማ መቆጣጠሩን ገለጸ

ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ከመደበኛው ጦር ጋር እያካሄደዉ ባለው ጦርነት ሌላ ከተማ መያዙን አስታውቋል።

በርካታ ሚዲያዎች በሰሜን ዳርፉር ግዛት ከቻድ ጋር በሚያዋስነው ድንበር አቅራቢያ በምትገኝ ከተማ ላይ የተፈጸመዉን የቅዳሜውን ጥቃት ማክሸፋቸውን ተናግረዋል።

በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ እና በሱዳን ጦር መካከል ያለው ጦርነት ከተጀመረ ወደ ሦስት ዓመት ገደማ የሆነው ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት ወደ አንዱ የዓለማችን አስከፊ ሰብአዊ ቀውስ አምርቷል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 11 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው እንደተፈናቀሉና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደተገደሉ ግምቱን አስቀምጧል፡፡

የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የሰሜን ዳርፉር ዋና ከተማ አል-ፋሽርን በጥቅምት ወር ከተቆጣጠረ በኋላ፤ በቻድ ድንበር አቅራቢያ በርካታ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርግ ቆይቷል።

ከሱዳን 18 ግዛቶች መካከል ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በሰሜን ዳርፉር በሠራዊቱ ቁጥጥር ሥር ካሉ አንዳንድ አካባቢዎች በስተቀር አምስቱን የምዕራብ ዳርፉር ግዛቶች ይቆጣጠራል።

መደበኛው ጦር ደግሞ ዋና ከተማዋን ካርቱምን ጨምሮ አብዛኞቹን ቀሪ ግዛቶች በቁጥጥሩ ሥር አድርጓል።

ባለፈው ሐሙስ የተባበሩት መንግሥታት የሱዳን ገለልተኛ እውነታ መርማሪ ልዑክ እንደገለጸው፤ የቡድኑ የከተማዋ ቁጥጥር ‹‹የዘር ማጥፋት ወንጀል ምልክቶች›› የታዩበት ነው ብሏል።

የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ይህን መግለጫ የሰጠዉ፤ የቡድኑ መሪ መሐመድ ሀምዳን ዳጋሎ በሱዳን ያለውን ግጭት ለማቆም ከኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ጋር ዓርብ ዕለት በኢንቴቤ ከተማ ከተወያየ በኋላ ነው ሲል አፍሪካ ኒዉስ ዘግቧል።

ሊዲያ ደሳለኝ

የካቲት 16/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *