በ2.4 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ 21 አዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የሚያደርገው ፕሮጀክት

በአፋር ክልል በአፍዴራና ዳሎል አካባቢ ላሉ የጨውና ፖታሽ አምራች ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም 21 አዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮችን 24 ሰዓት ተጠቃሚ የሚያደርግ የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ግንባታ ፕሮጀክት በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል ብሏል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ።

የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ በኢትዮጵያ ገንዘብ ከ2.4 ቢሊዮን ብር በላይ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ 16 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በአፍሪካ ልማት ባንክ እንዲሁም 84 ሚሊየን 627 ሺህ 401 ብር ደግሞ በተቋማችን በኩል የሚሸፈን ነው ተብሏል፡፡ 

ፕሮጀክቱ 375 ኪ.ሜ የመካከለኛ የኤሌክትሪክ መስመርና 93 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ እንዲሁም የ85 ትራንስፎርመሮች ተከላ ያካተተ ነው፡፡

እስካሁን በተከናወነው ስራ 278 ነጥብ 34 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመርና 33 ነጥብ 5 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ እንዲሁም የ29 ትራንስፎርመሮች ተከላ ተጠናቋል፡፡

በዚህም 8 መንደሮችንና አንድ ፋብሪካ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡

ይህ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ 14 ሺህ አባወራዎችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን፤ በአካባቢው ለሚገኙ ከ200 በላይ ወጣቶች ደግሞ የስራ እድል መፍጠር አስችሏል፡፡

አሁን ላይ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ አፈፃፀም 84 ነጥብ 46 ፐርሰንት የደረሰ ሲሆን፤ አጠቃላይ የፕሮጀክቱን ስራ በተያዘው በጀት ዓመት በማጠናቀቅ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት እንዲሰጥ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ፕሮጀክቱ በቀጣይም በአካባቢው በማዕድን ማውጣት ስራ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ የግል ድርጅቶችን በማበረታታትና የማህበረሰቡን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በማነቃቃት በቀጣይ ለሚከናወነው ሰፊ የኤሌክትሪክ ማዳረስ ስራ መሰረት የሚጥል ነው፡፡ 

በተጨማሪም በፕሮጀክቱ ወጪ በቀጣይ 17 አዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችል የግብአት አቅርቦት ግዢም ተፈፅሟል እንደ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መረጃ ።

የካቲት 18/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *