ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሉት ” ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ለይፋዊ ጉብኝት የመጡትን የእስራኤል ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግን ተቀብዬ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል።የኢትዮጵያ እና እስራኤልን ግንኙነት በማጤን በወል ፍላጎታችን ላይ ተመስርተን ትብብራችንን የምናሳድግባቸውን መንገዶች ተመልክተናል” ብለዋል።
የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሬዝዳንቱን ጉብኝት አስመልክቶ ባሰራጨው መረጃ፤ “ኢትዮጵያ አፍሪካ ውስጥ ወሳኝ አገር” እንደሆነች ገልጾ “በእስራኤል እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ትብብር፤ በአጠቃላይም ከአፍሪካ አገራት ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ትልቅ ምዕራፍ የሚከፍት ነው” ብሏል።
የካቲት 18/2018 ዓ.ም
