የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ከአሜሪካ ጋር ያላቸዉን ግንኙነት ለማሻሻል ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ፤የሀገሪቱ የኒውክሌር ባለቤትነት እውቅና ከተሰጠው ፒዮንግያንግ ከዋሽንግተን ጋር ያላትን ግንኙነት ማሻሻል ትችላለች ያሉ ሲሆን፤ ሴኡልን የሀገሪቱ ‹‹ጠላት››በማለት አቋማቸውን አጥብቀዋል።

የመሪው ንግግር የተሰማው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሚያዝያ ወር ወደ ቻይና ከሚያደርጉት ጉብኝት ጎን ለጎን ከኪም ጋር የመገናኘት ፍላጎት ሊኖራቸው ይችላል የሚል ግምት እየጨመረ በመጣበት ወቅት ነው።

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሀገራቸው ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ‹‹ተስማምታ መኖር››እንደምትችል የጠቆሙ ቢሆንም፤ የዋሽንግተን የጸጥታ አጋር የሆነችው ደቡብ ኮሪያ ግን አሁንም ‹‹ጠላት›› ሆና እንደቀጠለች መግለጻቸውን የመንግስት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ኪም ዋሽንግተን ለፒዮንግያንግ የኒውክሌር ኃይል ባለቤትነት እውቅና እንድትሰጥ አሳስበዋል።

የኮሪያ ማዕከላዊ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው፤ ኪም ‹‹ዋሽንግተን በሕገ-መንግሥቱ ውስጥ የተመለከተውን የሀገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ ካከበረች እና የጠላትነት ፖሊሲዋን ካነሳችከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በሰላም ላለመኖር ምንም ምክንያት የለም›› ብለዋል።

ፒዮንግያንግ በ2024 ደቡብ ኮሪያን ለመጀመሪያ ጊዜ ‹‹ጠላት ሀገር›› ብሎ ለመፈረጅ ሕገ-መንግሥቷን ማሻሻሏ ይታወሳል።

እስከዳር ግርማ

የካቲት 19/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *