ቻይና 70 በመቶ የሚሆነውን የነዳጅ ዘይት ከውጭ ታስገባለች ፡፡ ከግማሽ በላዩ በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ በኩል ነው የሚቀሳቀሰው ።የሀገሪቱ የነዳጅ ዘይት ምንጭ አብዛኛው ኢራን ነው፡፡
ነገር ግን ከአካባቢው ሌሎች አገሮች፣ ኢራቅ፣ ሳውዲ አረቢያ እና ኩዌትን ጨምሮ ይህንን ፍላጎቷን ታሟላለች፡፡
ቻይና ሁኔታው እየተባባሰ መሆኑ በእጅጎ አሳስቧታል ፡፡ደጋግማ እንደምትለውም ቀውሱ በከፍተኛ ስጋት እየተከታተለችው ነው።
ቻይና የአሜሪካ እና የእስራኤልን ድርጊት አጥብቃ አውግዛለች፡፡ በቅርቡ ከኢራን ጋር የተደረገው የኑክሌር ድርድር በትክክለኛው መንገድ ላይ ያለ ይመስላል ባይ ነች ።
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ሰኞ ዕለት ለኦማን፣ ኢራን እና ፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ንግግር አድርገዋል፡፡ በንግግራቸውም አሜሪካ እና እስራኤል ይህንን ዲፕሎማሲ ሆን ብለው በማዛባት ክልሉን ወደማይቀለበስ ቀውስ እንደከተቱት ደምድመዋል።
ቻይና የተኩስ አቁም ስምምነት እና ወደ ድርድር ጠረጴዛው መመለስን በተመለከተ አሁንም ጥሪዋን ማስተላለፍ ቀጥላለች።
ቤጂንግ በጉዳዩ ላይ ባወጣችው መግለጫ የኢራንን መንግስት ወዳጅ ብላ ጠርታዋለች ፡፡ ኢራን ግዛቷን እና ፍላጎቶቿን የመጠበቅ መብቷን እንደምትደግፍ ግልፅ አድርጋለች።
ዋንግ ዪ ቻይና ለኢራን የጦር መሳሪያ በማቅረብ ወይም ኢራንን በወታደራዊ መንገድ መርዳቷን ግን ሀሰት ብለዋል። ከዚህ ይልቅ ድጋፋችን ፖለቲካዊ እና ሞራላዊ ብቻ ነው ብለዋል ያለው አልጀዚራ ነው::
የካቲት 24/2018 ዓ.ም
