በአሜሪካ፣ በእስራኤል እና በኢራን መካከል የተቀሰቀሰው መጠነ ሰፊ ጦርነት አራተኛ ቀኑን በያዘበት በአሁኑ ወቅት፣ ግጭቱ ወደ መላው መካከለኛው ምስራቅ እየተስፋፋ መሆኑን የሚጠቁሙ አሳሳቢ ክስተቶች እየተመዘገቡ ይገኛሉ።
የአየር ድብደባ እና የድሮን ጥቃቶች፤
-እስራኤል በቴህራን እና በቤሩት በሚገኙ “የወታደራዊ ኢላማዎች” ላይ አዲስ እና መጠነ ሰፊ የአየር ድብደባ መፈጸሟን አስታውቃለች።
-በሌላ በኩል፣ በሳዑዲ ዓረቢያ የሚገኘውን የአሜሪካ ኤምባሲ በሁለት የኢራን ድሮኖች መመታቱን የሳዑዲ መከላከያ ሚኒስቴር ያረጋገጠ ሲሆን፤ በጥቃቱም “ውስን” የሆነ የቃጠሎ አደጋ ደርሷል።
-የኢራን መንግሥታዊ መገናኛ ብዙኃን በበኩላቸው፤በባህሬን በሚገኘው የአሜሪካ አየር ኃይል ጣቢያ ውስጥ የሚገኝ የአዛዥ እና የሠራተኞች ሕንፃ መውደሙን ዘግበዋል።
-የኢራን ባለሥልጣናት ለዓለም የኃይል አቅርቦት ወሳኝ በሆነው በሆርሙዝ የባሕር ሰርጥ በሚያልፉ መርከቦች ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ዝተዋል።
በዚህ መስመር ለማለፍ በሚሞክር ማንኛውም መርከብ ላይ ‹‹እሳት እንለኩሳለን››ሲሉ አንድ ከፍተኛ የኢራን ባለሥልጣን ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።
ፖለቲካዊ ውሳኔዎች እና ወታደራዊ ጉዳቶች፤
-የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፤ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቅዳሜውን ጥቃት “የመጨረሻው ዕድል” ሲሉ መግለጻቸዉን በመጥቀስ፤ ከባዱ የአሜሪካ ወታደራዊ ጥቃት ‹‹ገና ወደፊት ይመጣል›› ሲሉ ዝተዋል።
-የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር፤ከሰማይ በሚዘነብ ጥቃት የመንግሥት ለውጥ እንደሚመጣ አላምንም በማለት በፓርላማ ቢናገሩም፣ የአሜሪካ ጦር በኢራን በሚገኙ የሚሳኤል ጣቢያዎች ላይ ለሚያደርገው “የመከላከያ” ጥቃት ግን የብሪታንያ የጦር ሰፈሮችን እንዲጠቀም ፈቅደዋል።
የቢቢሲው ዓለም አቀፍ አርታኢ ጄረሚ ቦወን ሁኔታውን ሲያጠቃልሉ ፤ጦርነቱ ‹‹መቼ›› ወይም ‹‹እንዴት›› እንደሚጠናቀቅ መገመት ከባድ ነው ብለዋል።
ሀና ሰይፉ
የካቲት 24/2018 ዓ.ም
